Skip to main content
በአንድ ወቅት ነቢዩሏህ ሱለይማን ዐለይሂ ሰላም አንዲት ጉንዳን ከድንጋይ መኃል ያገኛሉ ። ጉንዳኗም አብሯት አንድ ፍሬ ስንዴ አጠገቧ ነበር ። ነቢ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም " እዚህ ድንጋይ መኃል እየኖርሽም አሏህ ይረዝቅሻልን ?! " ብለው ይጠይቋታል ። እርሷም " አዎን አሏህ ምን ይሳነዋል ?! " ብላ መለሰች ። " ለመሆኑ ይህች አንዷ የስንዴ ፍሬ ለምን ያክል ጊዜ ትበቃሻለች " ሲሉም ይጠይቋታል ። እርሷም " ለአንድ ዓመት ይበቃኛል !! " ስትል መለሰች ነቢዩ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም " እስቲ እኔ ዘንድ ለአንድ አመት ላቆይሽ " ብለው በመውሰድ አንድ የስንዴ ፍሬ ሰጥተው ያስቀምጧታል ። በአመቱም ጉንዳኗን ለማየት ወዳለችበት ሲሄዱ ግማሹን የስንዴ ፍሬ በልታ ግማሹን አስቀምጣዋለች ። ነቢዩ ሱለይማንም ተደንቀው " ለአንድ ዓመት አንድ የስንዴ ፍሬ ይበቃኛል ብለሽኝ አልነበረምን ?! ታዲያ ግማሹን በልተሽ ግማሹን ለምን ተውሽው ?! " ሲሉ በአግራሞት ይጠይቋታል ። እርሷም " መጀመሪያ ለአንድ አመት አንድ ፍሬ ስንዴ ይበቃኛል ያልኩት እኮ በአሏህ እጅ ላይ ሆኜ ነው !! አሁን ግን በአንንተ እጅ ስለገባሁ ሰው ነክና ልትረሳኝ ትችላለክ ብዬ ግማሹን በልቼ ግማሹን ደግሞ ለምናልባት ብዬ አስቀረሁት !! " ስትል መለሰችለት ። ከጉንዷን ብልህነትን እንማር ። ተስፋችን በአሏህ ላይ ይሁን ።
Popular posts from this blog
Comments
Post a Comment