Posts

Showing posts from April, 2021

ሰለምቴዋ ሰላማዊት ነኝ የእንዴት ሰለምኩኝ ታሪኬን ለቅምሻ ሹክ ማለትን ወደድኩኝ ። ነገሩ እንዲህ ነው ። ከቤታችን አዲስ ዲሽ እያስጫንን ነበርና የፊልም ጣቢያዎችን ስፈልግ ድንገት የአፍሪካ ቲቪ ቻናልን ተመለከትኩኝ ። በስህተት ነበር የተጫነው ይህ ቻናል ። እኔም በዛን ሰኣት በቲቪው የሚተላለፈውን ፕሮግራም መከታተል ጀመርኩኝ ።በዛን ጊዜ በሙሐመድ ካሚል ኑር የቀረበ ሲሆን ስለ ነቢዩ ሙሐመድ እዝነት ነበር የሚወራው። እርሱም ፦ይህንን ንግግር ነበር በድንገት ያደመጥኩት ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ ) ዘንድ አንድ ከገጠር የመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድኃ) ግለሰብ ሰሃን ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል ነቢዩም (ﷺ ) ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት ጀመሩ.. የመጀመሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ... ሁለተኛውንም ወይን ጎርሰው ፈገግ አሉ.. ያ ባለ ወይኑ የገጠሩ ሰው በነቢዩ ፈገግታ እጅጉን ተደሰተ.. የነቢዩ ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ (ﷺ) ስጦታ ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ.. የአላህ መልእክተኛ(ﷺ ) ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው ሰውም እጅግ በጣም ተደስቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት አመስግኖ ሄደ... አንድ የነቢይ (ﷺ) ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው ‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምን ነው ሳያካፍሉን.? አሏቸው !›› እሳቸውም ﷺ ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል አይደል?!..ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር.. ኮምጣጣ ነበር ባካፍላችሁ አንዳችሁ ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር እንዳታሳዩት ሰጋሁ..!!›› በማለት መለሱ ። ፊዳ'ከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱለሏህ ..!ﷺ ይህን ንግግር ሳበኝ ከዛም እምነቱን ለማወቅ ልቤ ተነሳሳ በዚሁ አጋጣሚ ኢሥላማዊ የቲቪ ቻናሎች እንዲጨመሩ አደረኩኝ ነሲሃ-ቲቪ ቻናልን አስጫንኩኝ መከታተልም ጀመርኩኝ ። ነሲሃ-ቲቪ አብዝሃኛውን ዳዕዋዎች እና ስለ ቁርኣን ነበር እያስተላለፈ ያለው ። እንግዲህ ለእሥልምናዬ የማስተዋል ሰበብ የሆነኝ ይህ ቢሆንም እሥልምናን ስቀበል ከቤት ተባርሬ በሰው ቤት ተቀጥሬ ለዲኔ ዋጋ ስከፍል ነበር ።ያም ሆኑ የሚገርመው እናቴ እህቴ ጎረቤቶችን እሥልምናን እንዲቀበሉ ሰበብ ሆኛለው ።መሉ ታሪኬ በአስሓቡል የሚን ሥር በዩቱብ ቻናላቸው በቅርብ ቀን የማቀርብ ይሆናል ። ሰላማዊት ታሪክ ለቅምሻ የተወሰደ ። እንዴት ወደ ቤተሰቦቿ በድጋሚ ልትመለስ ቻለች? እንዴት ቤተሰቦቿ እሥልምናን ሊቀበሉ ቻሉ ? ሰበቡ ምን ይሆን? ከዚህ አልፏ ወደ እውነት ጎዳና ጎረቤትን ሁሉ እየጠራች በራቸው እያንኳኳች ትገቻለች ። ሙሉ ታሪክ በቅርብ ቀን ............... https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q ቤተሰብ ይሁኑ አሁንም ባለ ታሪክ ለሆኑ ሰለምቴዎች በራችን ክፍት ነው ይላል የአስሓቡል የሚን ጀመዐ ። ሰለምቴዎችን እንጋብዛለን ። እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮን ያካፍሉን ። አድራሻችን ፦ የሰለምቴዎች ግሩፕ http://t.me/Selmeta ቴሌግራም 00966597257492 http://t.me/Ohanw9 እህት ሐድል 00966503917209 http://t.me/OBintMahmud እህት የትም ወርቅ በዋትስ-አፕ 00966554225870 https://t.me/Quran_is_life_Sari_A እህት ሳራ ቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/AshaBuleyamine የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ፦ https://m.youtube.com/watch?v=ssov6TY3yzc&feature=youtu.be ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Image

ነገ የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን ማሟያ ነው! በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳደረሱን በተሚዝ አካባቢ ያለው የጨረቃ መጠባበቂያ ማእከል ውጤት ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን ሆኖም ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ ሰኞ ሚያዝያ 4/2013 የረመዳን ዋዜማ የሻዕባን የመጨረሻ ቀን ይሆናል። ማክሰኞ ደግሞ ረመዳን 1 ይሆናል። ከሳውዲ ከፍተኛ ፍርድቤት ይፋ መግለጫ በመጠበቅ ላይ ነው። ነሲሓ ቲቪ መላውን ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያለ አላህ ተውበትና መልካም ስራን እንዲያገራልን እንለምነዋለን። ረመዳን ሙባረክ! ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉን 👇 https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Image

AS-HABULE YAMINE Family Ramadan Mubarak 🌘 كل عم وانتم بالف خير https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

Image

በአንድ ወቅት ነቢዩሏህ ሱለይማን ዐለይሂ ሰላም አንዲት ጉንዳን ከድንጋይ መኃል ያገኛሉ ። ጉንዳኗም አብሯት አንድ ፍሬ ስንዴ አጠገቧ ነበር ። ነቢ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም " እዚህ ድንጋይ መኃል እየኖርሽም አሏህ ይረዝቅሻልን ?! " ብለው ይጠይቋታል ። እርሷም " አዎን አሏህ ምን ይሳነዋል ?! " ብላ መለሰች ። " ለመሆኑ ይህች አንዷ የስንዴ ፍሬ ለምን ያክል ጊዜ ትበቃሻለች " ሲሉም ይጠይቋታል ። እርሷም " ለአንድ ዓመት ይበቃኛል !! " ስትል መለሰች ነቢዩ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም " እስቲ እኔ ዘንድ ለአንድ አመት ላቆይሽ " ብለው በመውሰድ አንድ የስንዴ ፍሬ ሰጥተው ያስቀምጧታል ። በአመቱም ጉንዳኗን ለማየት ወዳለችበት ሲሄዱ ግማሹን የስንዴ ፍሬ በልታ ግማሹን አስቀምጣዋለች ። ነቢዩ ሱለይማንም ተደንቀው " ለአንድ ዓመት አንድ የስንዴ ፍሬ ይበቃኛል ብለሽኝ አልነበረምን ?! ታዲያ ግማሹን በልተሽ ግማሹን ለምን ተውሽው ?! " ሲሉ በአግራሞት ይጠይቋታል ። እርሷም " መጀመሪያ ለአንድ አመት አንድ ፍሬ ስንዴ ይበቃኛል ያልኩት እኮ በአሏህ እጅ ላይ ሆኜ ነው !! አሁን ግን በአንንተ እጅ ስለገባሁ ሰው ነክና ልትረሳኝ ትችላለክ ብዬ ግማሹን በልቼ ግማሹን ደግሞ ለምናልባት ብዬ አስቀረሁት !! " ስትል መለሰችለት ። ከጉንዷን ብልህነትን እንማር ። ተስፋችን በአሏህ ላይ ይሁን ።

Image

እስልምናን ለማጥቃት ሲል ግን በእስልምና የተማረከው ጀግና..! ክፍል 1 ዛሬ እስኪ አንድ ጀግና ላስተዋዉቃችሁ እስልምናን ለማጥቃት ሲል ግን በኢስላም የተማረከ ጀግና share አድርጉት በልጅነት እናትና አባቱ ከአገር ይወጣሉ። በዚህ አጋጣሚ በእናቱ እናትና አባት በአያቶቹ እጅ ያድጋል። ክርስትናም አዲሱ ገበያ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ያስጠምቁታል። በልደታ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ አንድ ፕሮቴስታንት ኢየሱስ ጌታ ነው እያለ ሲሰብክ ቴሌ የቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ገፍትረው በድንጋይ የማርያም ጠላት እየተባለ በድንጋይ ወግረው ሲገሉት ያያል። በመቀጠል ጎፋ ገብርኤል ደጅ ላይ ድግምት የተሰራበት ሰው እንቁራሪት ሲያስታውክ ያያል። ያንን ድርጊት ሲያይ በቀጥታ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይሰናበታል። በመቀጠል ኢየሱስ ጌታ ነው ወደሚሉት ፕሮቴስታንት ሰሜን መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በመነጋገር ኢየሱስን የግል አዳኙ አድርጎ ተቀበለ። የደህንነት ትምህርት ከተማረ በስድስት ወሩ የውኃ ጥምቀት ወስዶ ተከታታይ ኮርስ ወሰደ። በዚህ ወቅት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በግሉ ማንበብ እና የተለያዩ ማብራሪያዎችን መመልከት ጀመረ። ይህንን የአብነት ትምህርት እየተማረ በተጓዳኝ የአስኳላ ትምህርት ኢለመንተርይ ጨርሶ ሃይስኩል ገባ። ከዚያ ከሃይስኩል ወደ ፕሪፓቶቴርይ ከፕሪፓራቶሪ ወደ አምስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ቅርንጫፍ ወደሆነ የህንጻ ምህንድስና 5 ዓመት ካጠናቀቀ በኃላ። ከአገር ይወጣል። ካገር ከወጣ በኃላ ስቶክሆል ዩንቨርስቲ በማቴሪያል ኢንጅነሪንግ እየተማረ እያለ በግቢ ውስጥ በሚደረገው የፍልስፍና የስነ ልቦና እና የስነ አመክንዮ ውይይት ላይ መሳተፍ ጀመረ። አንድ ጓደኛው ፓል ቶክ የሚባል የውይይት መድረክ አለ እዛ ገብተህ ብታተረማምሳቸው ጥሩ ነበር አለው። ወደ ሳይበሩ ዓለም ሲመጣ አጋጣሚ ክርስትና እና እስልምና የሚፋጠጡበት መድረክ ነበር። ከኢትዮጵያ ኡስታዝ አቡሃይደር ከፈረንሳይ በረከት የሚባሉ ጠንካራ ተወያዮች ሁለት የተለያየ ግሩፕ መስርተው ይወያዩ ነበር። በዚህ ወቅት ነው የክርስትናውን መድረክ የተቀላቀለው። ይቀጥላል...... እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮን ያካፍሉን ። አድራሻችን ፦ http://t.me/Selmeta ቴሌግራም 00966597257492 http://t.me/Ohanw9 00966503917209 http://t.me/OBintMahmud በዋትስ-አፕ 00966554225870 https://t.me/Quran_is_life_Sari_A የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ https://youtu.be/aU23u6NuZTo የአስሓቡል የሚን ማህደር፦ https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን።

Image

ማህሌት ነኝ ሰለምቴዋ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ። እርሱም ወደ ተፈጠርኩበት እምነት እንድመለስ ያደረገኝ አጋጣሚ ቢኖር ። በአንድ አጋጣሚ የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ትምህርት ተፓስቶ አሳዛኝና አስለቃሽ ታሪክ የሚል አርእስት ተመለከትኩኝ እና ምንድን ነው ብዬ ቪድዮውን ከፍቼ ማድመጥ ጀመርኩኝ ። ከዚህ በፊት እኔ ለእሥልምና መጥፎ አመለካከት ያለኝ ልጅ አልነበርኩም ። ማለት እምነቱ ትክክል ነው የማለት እሳቤው ባይኖረኝም ግን የሰውን እምነት ስለማከብር ያለ እውቀት በሰዎች እምነት ላይ ድንበር ዘለልና ጥላቻን ያዘለ ቃላቶችን እና መጥፎ አመለካከት የለኝም ነበር ። ይህም የሰው እምነት ስለሆነ ክብር እሰጣለው ። ወደ ጀምሬ ልመለስና ቪድዮውን ማድመጥ ጀመርኩኝ ኡስታዝ ያሲን ሲናገር አይኖቹ ከእንባ አልደረቁም ነበር እያለቀሰ ታሪኩኝ ጀመረ ታሪኩ ሁሉን ነገር ጥሎ ወደ ነቢያችን ሥለ መጣ ሰው ነበር እርሱም የጆንያው ባለቤት የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን ያንን ጊዜ የእኔም ህይወት ተቀየረ ንግግሩን እያደመጥኩኝ በእንባ ታጅቤ አይኖቼ ያነባሉ ። ምንድን ነው ? አልኩኝ እራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ ማህሌት ምንድን ነው ያስለቀሰሽ ብዬ ውስጤን ጠየኩኝ የልቤ ትርታ ጨመረ ረሱልን ልቤ መፈለግና ማወቅ አሰበ በቃ ነገሮች ምትት አሉብኝ ። ስለ ጆንያው ባለቤት እዲህ እያለ ነበር ኡስታዝ ማውራት የጀመረው ፦ #የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን(ረ.ዐ) አጭር የህይወት ታሪክ ። እስልምናን በመቀበሉ ብቻ የለበሰውን ልብስ እንኳን ሳይቀር በአጎቱ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ ጆንያ ለብሶ የናፈቃቸውን ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለማግኘት ጉዞውን ወደ መዲና አደረገ ልክ መዲና ሲደርስ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቤት በር ላይ ቆሞ የነሱ ከቤት መውጣት በናፍቆት ይጠባበቅ ጀመር ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከቤት ሲወጡ ባየ ጊዜ የደስታ እንባው ጉንጩ ላይ መፍሰስ ጀመረ የናፈቃቸውን ወዳጆቹን እና ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሶላት አሰግደው እንደጨረሱ እንደ ልምዳቸው ቆሙ እና ማን ሰገደ ማን ቀረ እያሉ የባልደረቦቻቸውን ፊት ማስተዋል ጀመሩ፦ ከዛ ይሄንን ወጣት አዩት ከየት ነው የመጣህ አንተ ወጣት ብለው ጠየቁት እርሱም ከሙዘይና ጎሳ ነው ሸሽቼ የመጣሁት አሏቸው፦ ነብዩ ስምህ ማነው አሉት አብዱል_ኡዛ(የኡዛ_ባርያ) እባላለሁ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተገርመው አዩት እና ይሄ የለበስከው ጆንያ ምንድነው ልብስ የለህም ብለው ጠየቁት፦ እርሱም አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አጎቴ በእርሶ መስለሜን ባወቀ ጊዜ ያለኝን ንብረቴን ሁሉ ቀማኝ ከነዚህ ጆንያዎች ውጪ ምንም አላገኘሁም አንተን ለመገናኘት ስል ላይ እና ታች አስሬ ወደ አንተ መጣሁ የአላህ መልእክተኛ አሏቸው፦ ነቢዩ ﷺ ይህንን አደረክ እንዴ አንተ ለአላህ እና መልእክተኛው ስትል ንብረትህን ጥለህ መጣ አላህ በነዚህ ሁለት ጆንያዎች ልብስ ይስጥህ ጀነት ውስጥ የፈለከውን እየበላህ የፈለከውን ለብሰህ ኑር በጀነት ውስጥ አንተ ከአሁን በኋላ #አብዱል_ኡዛ አይደለህም #ዙል_ቢጃደይን ነህ የጆንያዎች ባለቤት ነው ስምህ ። ኡላሞች ይሄ ሰው የውመል ቂያማ መክሉቃታ በአላህ ፊት በቆመበት ፊት ይጠራል አንተ ዙል ቢጃደይን ውጣ ወደ አላህ ይባላል ። ዙል ቢጃደይን ንብረቱን ሁሉ ነገሩን ትቶ ወደ ነቢዩ ﷺሸሸ እራቁቱን እሳቸው ጋር ተገናኘ አህለ ሶፋ የሚባሉ ነቢዩ ﷺሶሃባዎች ደሀዎች ከነብዩ ቤት ጀርባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ ከነሱ ጋር መኖር ጀመረ ይሄ ሶሃባ ። አብዱል ኡዛ የዛሬው አድሱ ስሙ አብደላህ ዙል ቢጃደይን ይባላል አብደላህ ከሰለመ በኋላ የአላህ ሱብሃናሁ ወተአላ ትልቅ ባርያ ሆነ ከኢባዳዎቹ ውስጥ በጣም ዱዓ እና ዚክር ያበዛ ነበር፦ ተመላሹ ተፀፃቹ ብለው ነበር ስሙን የሚጠሩት ሌላው ባህሪው ቁርአን መቅራት በጣም ያበዛ ነበር ። በቃ ይህንን ታሪክ ካደመጥኩኝ በኋላ ውስጤ ተረበሸ ማድመጥም ማንበብም አለብኝ ብዬ ተነሳሁኝ ነገሮችን ትኩረት ሰጥቼ በሃይማኖት ትምህርት ላይ ትኩረት አደረኩኝ አሏህ የኡስታዝን ንግግር ሰበብና የማንቂያ ደውል አደረገልኝ እኔም ብዙዎችን የሃይማኖት ስብከትን እና ከማንበብ ከማድመጥ በኋላ ወደ ተፈጠርኩበት እምነት ብሸሃዳተይን ገባሁኝ ። አሁን አልሃምዱሊላህ የተረጋጋ መንፈስ እና ደስ የሚል ህይወት ውስጥ ነው ። መልእክት ቢኖረኝ አንብቡ ትምህርቶችን አድምጡ ከእውቀት ጋር እውነትም ትገለጥላችኃለች ነው 🙏 አሏህ ከፈቀደና ነገሮች ሲመቻቹልኝ በድምጽ በደንብ አድርጌ ታሪኬን ላካፍላችሁ እወዳለሁ ። ኢንሻሏህ ✍️ https://t.me/joinchat/RXYpviFTL70OQdu2 አሁንም ባለ ታሪክ ለሆኑ ሰለምቴዎች በራችን ክፍት ነው ይላል የአስሓቡል የሚን ጀመዐ ። ሰለምቴዎችን እንጋብዛለን ። እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮን ያካፍሉን ። አድራሻችን ፦ የሰለምቴዎች ግሩፕ http://t.me/Selmeta ቴሌግራም 00966597257492 http://t.me/Ohanw9 00966503917209 http://t.me/OBintMahmud በዋትስ-አፕ 00966554225870 https://t.me/Quran_is_life_Sari_A ቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/AshaBuleyamine የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ፦ https://m.youtube.com/watch?v=ssov6TY3yzc&feature=youtu.be ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን።

Image

ጉዞ ወደ ኢሥላም ❤️ አልሃምዱሊሏህ እህታችን በሸሃዳተይን ወደ እሥልምና ገብታለች

Image

ከወንድም አቡበከር ትረካ የተወሰደ አቢ ደምደም ማን ነው ? እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማን ነዉ?? _________ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው የብዙዎቻችሁ ጥያቄ እንደሚሆን እገምታለሁ ተከተሉኝማ ልንገራችሁ። አቡ ዳዉድና ጦብራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድያላሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸዉ ከእናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማነው ?? በማለት ጠየቋቸው ሰሀቦችም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው በማለት በግርምት ጠየቋቸው ። እሱማ አሉ ነብያችን ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት ጌታየ ሆይ እኔ ነብሴና ክብሬን ሰጥቸሀለሁ የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሰድብም። የበደሉትን አይበድልም የሚመቱትንም መልሶ አይመታም አሏቸው የአቢ ደምደምና የአባታችን አደም አለይሂ ሰላም ልጅ ታሪካቸው ተመሳሳይነት አለው። ወንድሙ ሊገድለው በዛተበት ወቅት እንዲህ በማለት ነበር የመለሰለት ። ልትገድለኝ እጅህን ወደኔ ብትዘረጋ እኔ ልገድልህ እጀን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም እኔ የአለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁና አለ ። አቢ ደምደም ታሪኩ አጭር ቢሆንም ከስብዕናው የምናገኘው መልዕክት ግን ግዙፍ ነው በዋናነት ከምፅዋት ወይም ሰደቃ ምንም የሚሰጠው ነገር የለለው ሰው ስምና ክብሩን አሳልፎ በመስጠት ብቻ እሱን ያሙ ሰዎች ወንጀል ዉስጥ እንዳይወድቁ ዋስትናን ሊሰጣቸው እንደሚችልም እንማራለን ። ቢያሙኝም በኔ ምክንያት መጠየቅ የለባቸውም ስጋየ ለነሱ ሀላል ነዉ የሚል ይመስላል አቢ ደምደም። ወዳጆቸ በኔ ምክንያት አንድም ሰዉ መጠየቅ የለበትም ማለት ምንኛ ለሰው ልጅ ማዘንና መቆርቆር ነዉ። የዘመናችን የሰብዓዊ መብት ታጋዮችስ ይህን ያህል ተጉዘው ይሆን? ብቻ የአቢ ደምደም ነገር ይገርማል በምፅዋት ወይም ልግስና ዙሪያ ታዋቂው ኢማም ኢብኑል ቀዩም ሲናገሩ ልግስና አስር ደረጃዎች አሉት ካሉ በኋላ ከነዚህ መካከል የራስን ክብርና ስም መስጠትን በሰባተኛ ደረጃ ላይ ቆጥረዋል ። ወዳጆቼ ሆይ የአቢ ደምደምን ሁኔታ ሳስበው ዉስጡ እንዲህ የሚል መሰለኝ ጌታየ ሆይ ሰዎች ሁሉ ከገንዘብ እና ንብረት የሚለግሱት ነገር አላቸው እኔ ግን የምሰጠውም የምለግሰዉም ነገር የለኝምና ይህንኑ ስጦታየን ተቀበለኝ የሰደበኝና ያማኝን ሰዉ ሁሉ ነፃ ነህ ዕዳ የለብህም በኔ ምክንያት አትቀጣም ብየዋለሁ ። ታዲያ ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም በአቢ ደምደም ሁኔታ በመደነቅ ይመስላል ማነው ከእናንተ ዉስጥ መሆን የሚችለው በማለት የሚጠይቁት በእርግጥ ነገሩ አላህ ሱበሀነወ ተአላ ላገራለት ሰው ካልሆነ በስተቀር እጅግ ከባድ ነው ። ወዳጆቸ ሆይ አንዳንድ ጊዜ ባላሰብነዉ መልኩ ከግብራችን ጋር የማይዛመዱ ስም ሊሰጠን ይችላል ለማስተካከል ስንወድቅ ስንነሳ ለድናችን ስንሮጥ ለዑማዉ ስንታትር ስንፅፍ ስንናገር ስንከራከር ፈፅሞ የማይመስልና ያልጠበቅነውን ነገር ልንባል እንችላለን ። ያላንዳች ጥቅም የማንሮጥ ተደርጎም ሊወራብን ይችላል እዉነተኛ የአላህን ዉዴታ ፈልገንና ለድኑ አስበን የምንሰራ ከሆነ ምንም እንኳን የሚወጡልንና የሚሰጡን ስሞች ከባድ አሳማሚና አስደንጋጭ ቢሆኑም ፈፅሞ ልንሸበር አይገባም ባይሆን እንደ አቢ ደምደም እንሁን ። የሰደበንን መልሰን አንስደብ የበደለንን አንበድል የመታንን ለመምታት አንጋበዝ ከማሀይማን ጋር ጊዜ አናጥፋ። እነሱ አላወቁም ና ይቅር እንበላቸው ያኔ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም አለም ስኬት እንጎናፀፋለን ። እንደ አቢ ደምደም እንሁን ሰው እንዲህ አለኝ ብለን አንጨነቅ ሰዉ ስላለ አይሙቀን ሰዉ ስላላለም አይብረደን ደረታችን ትግስታችን ፅናታችን ይቅርታችን ሰፊ ይሁን ። የበደሉን ሰዎች ካሉ የመጀመሪያዎቹ ተጎጅዎች እነሱ ራሳቸው ናቸውና እንዘንላቸዉ። ላጠፉብን ይቅር እንበላቸው ከይቅርታ በላይ ጣፋጭ ነገር የለምና ወዳጆቸ ሆይ ከድርጊት በፊት የነገሮችን ትርፍና ኪሳራ ከወዲሁ መገመትና ማመዛዘን ብልህነት ነው ። አዎን የዋህነት ሞኝነት አይደለም ። መታገስና መፍራት የተለያዩ ነገሮች ናቸው በትንሹ በትልቁ ከሰዎች ጋር መጋጨት ከመሀይማን ጋር መጣላትና መልስ መሰጣጠት የጥሩ አማኝ ባህሪ አይደለም ። ምንም ለነገሮች መስጠት የሚቻል ቢሆንም ሰምቶ መቻናልና ንቆ መተዉ ለበለጠ ዉጤት የሚያበቃ ከመሆኑም በላይ የበሳልነት ምልክት ነዉ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg

Image