ለእሥልምና ትልቅ ጥላቻ ነበረኝ ያለው ሰለምቴው አባስ በባጢል ላይ ያሳለፋቸው ጊዜኣቶች እየተቆጨባቸው ወደ ኢሥላም በመምጣቱ በሐሴት ተሞልቶ የእሥልምናን ጣፋጭ መዓዛ እየናገረ ዛሬ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ላይ ከወንድም ሙሐመድ ጋር ቆይታውን በማድረግ ድንቅ ታሪኩን አካፍሎናል ። 👇 https://m.youtube.com/watch?v=2QFdvrYfr3k&feature=youtu.be የሰለምቴዎች የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በአዲስ ታሪክ ከአዲስ እንግዳ ጋር ይቀጥላል......... AS-HABULE YAMLNE TUBE https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

Comments

Popular posts from this blog

እስልምናን ለማጥቃት ሲል ግን በእስልምና የተማረከው ጀግና..! ክፍል 1 ዛሬ እስኪ አንድ ጀግና ላስተዋዉቃችሁ እስልምናን ለማጥቃት ሲል ግን በኢስላም የተማረከ ጀግና share አድርጉት በልጅነት እናትና አባቱ ከአገር ይወጣሉ። በዚህ አጋጣሚ በእናቱ እናትና አባት በአያቶቹ እጅ ያድጋል። ክርስትናም አዲሱ ገበያ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ያስጠምቁታል። በልደታ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ አንድ ፕሮቴስታንት ኢየሱስ ጌታ ነው እያለ ሲሰብክ ቴሌ የቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ገፍትረው በድንጋይ የማርያም ጠላት እየተባለ በድንጋይ ወግረው ሲገሉት ያያል። በመቀጠል ጎፋ ገብርኤል ደጅ ላይ ድግምት የተሰራበት ሰው እንቁራሪት ሲያስታውክ ያያል። ያንን ድርጊት ሲያይ በቀጥታ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይሰናበታል። በመቀጠል ኢየሱስ ጌታ ነው ወደሚሉት ፕሮቴስታንት ሰሜን መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በመነጋገር ኢየሱስን የግል አዳኙ አድርጎ ተቀበለ። የደህንነት ትምህርት ከተማረ በስድስት ወሩ የውኃ ጥምቀት ወስዶ ተከታታይ ኮርስ ወሰደ። በዚህ ወቅት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በግሉ ማንበብ እና የተለያዩ ማብራሪያዎችን መመልከት ጀመረ። ይህንን የአብነት ትምህርት እየተማረ በተጓዳኝ የአስኳላ ትምህርት ኢለመንተርይ ጨርሶ ሃይስኩል ገባ። ከዚያ ከሃይስኩል ወደ ፕሪፓቶቴርይ ከፕሪፓራቶሪ ወደ አምስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ቅርንጫፍ ወደሆነ የህንጻ ምህንድስና 5 ዓመት ካጠናቀቀ በኃላ። ከአገር ይወጣል። ካገር ከወጣ በኃላ ስቶክሆል ዩንቨርስቲ በማቴሪያል ኢንጅነሪንግ እየተማረ እያለ በግቢ ውስጥ በሚደረገው የፍልስፍና የስነ ልቦና እና የስነ አመክንዮ ውይይት ላይ መሳተፍ ጀመረ። አንድ ጓደኛው ፓል ቶክ የሚባል የውይይት መድረክ አለ እዛ ገብተህ ብታተረማምሳቸው ጥሩ ነበር አለው። ወደ ሳይበሩ ዓለም ሲመጣ አጋጣሚ ክርስትና እና እስልምና የሚፋጠጡበት መድረክ ነበር። ከኢትዮጵያ ኡስታዝ አቡሃይደር ከፈረንሳይ በረከት የሚባሉ ጠንካራ ተወያዮች ሁለት የተለያየ ግሩፕ መስርተው ይወያዩ ነበር። በዚህ ወቅት ነው የክርስትናውን መድረክ የተቀላቀለው። ይቀጥላል...... እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮን ያካፍሉን ። አድራሻችን ፦ http://t.me/Selmeta ቴሌግራም 00966597257492 http://t.me/Ohanw9 00966503917209 http://t.me/OBintMahmud በዋትስ-አፕ 00966554225870 https://t.me/Quran_is_life_Sari_A የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ https://youtu.be/aU23u6NuZTo የአስሓቡል የሚን ማህደር፦ https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን።

ሰለምቴው አብዲሳ.....! እሥልምና መርጦኛል ። ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ አስላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ የአስሓቡል የሚን ቤተሰቦች ። ስሜ አብዲሳ እምሩ ይባላል የምኖረው በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ(አሰበ ተፈሪ) ሲሆን በአሏህ እዝነት ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደጃለው አሏህ በራህመቱ በ2010 የኦርቶዶክስ ፆም ውስጥ ነበር የሰለምኩት(ከክህደት አለም የወጣሁት) ነገሩ ወዲህ ነው ስምንተኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ የኖርኩት ካፊሮች (ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች) የሚበዙበት ሰፈር ነው ግን ልክ 2008 አካባቢ ስምንተኛ ክፍል ሳለው ሙስሊሞች ሚበዙበት ሰፈር 90% የሚሆኑት የሰፈሩ ነዋሪዎች ሙስሊም የሆኑ ሰፈር ገባን ሁለት አመት እዛ ከኖርን በኃላ ከሰፈሩ ሰው እየተላመድን ስንመጣ እኔም ከሙስሊም ልጆች ጋር ጓደኝነት ጀመርኩ ይሄን ጊዜ ነው እንግዲ የሂዳያ ስጦታዬን ለማግኘት ጉዞ የጀመርኩት። ለጥናት ከሙስሊም ልጆች ጋር በምንገናኝበት ጊዜ ስለእምነት Discuss እናደርግ ነበር ።አንዳንዴም የከፋ ሙግት አደርግ ነበር! ከሙስሊም ጓደኞቼ ሀዲሶችን እሰማ ነበር ብዙ ጊዜ የእየሱስ ክርስቶስ (ነቢ ኢሳ) አሌይሂ ሰላም አልሞተም አልተሰቀለም የምትለዋን ነገር ስሰማ በጣም እናደድ ነበር። አንዳንድ ቀን ለብቻዬን ቁጭ ብዬ ልስለም አልስለም ብዬ ከአእምሮዬ ጋር ግጥሚያ ጀመርኩ ........."አሁን ልስለም ብል ቤተሰቦቼን ትቼ ነው ምሰልመው አይ ይቅርብኝ እነሱን ትቼ ከምሰልም ይቅርብኝ አይ" ብዬ ከአእምሮዬ ጋር ከባድ ጦርነት ገጥም ነበር ግን ከእለታት አንድ ቀን የህይወቴ turning point (ህይወቴ የተለወጠበት) ቀን ላይ ደረስኩ ትዝ ይለኛልእኔ እና ሁለት የሙስሊም ጓደኞቼ ቁጭ ብለን ባለንበት ምላሴ ከአእምሮዬ ጋር ሳይማከር በድንገት ሙስሊም መሆን ፈልጋለው የሚል ቃል ተናገረ! ከዛ እነሱም የሰሙትን ማመን አቅቷቸው እ እ እያሉ በግርምት ያዩኝ ጀመር እኔም በድጋሚ አው ሙስሊም ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ጠየኳቸው እነሱም ምንም ማድረግ አይጠበቅብህም ሸሀዳ ብቻ ማለት ነው ሚያስፈልግህ ከአንገቴ ላይ የሺርክ ገመድን(መስቀል) ፈትቼ ሸሀዳ (መሬት ላይ ያለ ነገር በሙሉ የሷን ያህል መመዘን የማይችለውን ቃል) አልኩኝ በአሏህ እዝነት አልሀምዱሊላህ ወደ ተወለድኩበት እምነት ወደ እስልምና ተመለስኩ ወርቃማ ብዬ መግለፅ ማልችለው ስጦታ ከአሏህ ተበረከተልኝ............. .ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል አብዲሳ ነኝ ሠለምቴው ። ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ የሠለምቴዎችን ታሪክ ለመከታተል ይወዳጁን ዩቱብ https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q ቴሌግራም http://t.me/AshaBuleyamine የፌስ-ቡክ ገጽ https://www.facebook.com/Ashabuleyamine/ አስተያየት ካሎት በድምጽም ሆነ በጹሑፍ መልክ ያስቀምጡ ይደርሰናል 👇 http://t.me//Ashabulyeminbot የሠለምቴዎች እንግዳ መቀበያ http://t.me/Selmeta

ከወንድም አቡበከር ትረካ የተወሰደ አቢ ደምደም ማን ነው ? እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማን ነዉ?? _________ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው የብዙዎቻችሁ ጥያቄ እንደሚሆን እገምታለሁ ተከተሉኝማ ልንገራችሁ። አቡ ዳዉድና ጦብራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድያላሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸዉ ከእናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማነው ?? በማለት ጠየቋቸው ሰሀቦችም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው በማለት በግርምት ጠየቋቸው ። እሱማ አሉ ነብያችን ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት ጌታየ ሆይ እኔ ነብሴና ክብሬን ሰጥቸሀለሁ የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሰድብም። የበደሉትን አይበድልም የሚመቱትንም መልሶ አይመታም አሏቸው የአቢ ደምደምና የአባታችን አደም አለይሂ ሰላም ልጅ ታሪካቸው ተመሳሳይነት አለው። ወንድሙ ሊገድለው በዛተበት ወቅት እንዲህ በማለት ነበር የመለሰለት ። ልትገድለኝ እጅህን ወደኔ ብትዘረጋ እኔ ልገድልህ እጀን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም እኔ የአለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁና አለ ። አቢ ደምደም ታሪኩ አጭር ቢሆንም ከስብዕናው የምናገኘው መልዕክት ግን ግዙፍ ነው በዋናነት ከምፅዋት ወይም ሰደቃ ምንም የሚሰጠው ነገር የለለው ሰው ስምና ክብሩን አሳልፎ በመስጠት ብቻ እሱን ያሙ ሰዎች ወንጀል ዉስጥ እንዳይወድቁ ዋስትናን ሊሰጣቸው እንደሚችልም እንማራለን ። ቢያሙኝም በኔ ምክንያት መጠየቅ የለባቸውም ስጋየ ለነሱ ሀላል ነዉ የሚል ይመስላል አቢ ደምደም። ወዳጆቸ በኔ ምክንያት አንድም ሰዉ መጠየቅ የለበትም ማለት ምንኛ ለሰው ልጅ ማዘንና መቆርቆር ነዉ። የዘመናችን የሰብዓዊ መብት ታጋዮችስ ይህን ያህል ተጉዘው ይሆን? ብቻ የአቢ ደምደም ነገር ይገርማል በምፅዋት ወይም ልግስና ዙሪያ ታዋቂው ኢማም ኢብኑል ቀዩም ሲናገሩ ልግስና አስር ደረጃዎች አሉት ካሉ በኋላ ከነዚህ መካከል የራስን ክብርና ስም መስጠትን በሰባተኛ ደረጃ ላይ ቆጥረዋል ። ወዳጆቼ ሆይ የአቢ ደምደምን ሁኔታ ሳስበው ዉስጡ እንዲህ የሚል መሰለኝ ጌታየ ሆይ ሰዎች ሁሉ ከገንዘብ እና ንብረት የሚለግሱት ነገር አላቸው እኔ ግን የምሰጠውም የምለግሰዉም ነገር የለኝምና ይህንኑ ስጦታየን ተቀበለኝ የሰደበኝና ያማኝን ሰዉ ሁሉ ነፃ ነህ ዕዳ የለብህም በኔ ምክንያት አትቀጣም ብየዋለሁ ። ታዲያ ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም በአቢ ደምደም ሁኔታ በመደነቅ ይመስላል ማነው ከእናንተ ዉስጥ መሆን የሚችለው በማለት የሚጠይቁት በእርግጥ ነገሩ አላህ ሱበሀነወ ተአላ ላገራለት ሰው ካልሆነ በስተቀር እጅግ ከባድ ነው ። ወዳጆቸ ሆይ አንዳንድ ጊዜ ባላሰብነዉ መልኩ ከግብራችን ጋር የማይዛመዱ ስም ሊሰጠን ይችላል ለማስተካከል ስንወድቅ ስንነሳ ለድናችን ስንሮጥ ለዑማዉ ስንታትር ስንፅፍ ስንናገር ስንከራከር ፈፅሞ የማይመስልና ያልጠበቅነውን ነገር ልንባል እንችላለን ። ያላንዳች ጥቅም የማንሮጥ ተደርጎም ሊወራብን ይችላል እዉነተኛ የአላህን ዉዴታ ፈልገንና ለድኑ አስበን የምንሰራ ከሆነ ምንም እንኳን የሚወጡልንና የሚሰጡን ስሞች ከባድ አሳማሚና አስደንጋጭ ቢሆኑም ፈፅሞ ልንሸበር አይገባም ባይሆን እንደ አቢ ደምደም እንሁን ። የሰደበንን መልሰን አንስደብ የበደለንን አንበድል የመታንን ለመምታት አንጋበዝ ከማሀይማን ጋር ጊዜ አናጥፋ። እነሱ አላወቁም ና ይቅር እንበላቸው ያኔ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም አለም ስኬት እንጎናፀፋለን ። እንደ አቢ ደምደም እንሁን ሰው እንዲህ አለኝ ብለን አንጨነቅ ሰዉ ስላለ አይሙቀን ሰዉ ስላላለም አይብረደን ደረታችን ትግስታችን ፅናታችን ይቅርታችን ሰፊ ይሁን ። የበደሉን ሰዎች ካሉ የመጀመሪያዎቹ ተጎጅዎች እነሱ ራሳቸው ናቸውና እንዘንላቸዉ። ላጠፉብን ይቅር እንበላቸው ከይቅርታ በላይ ጣፋጭ ነገር የለምና ወዳጆቸ ሆይ ከድርጊት በፊት የነገሮችን ትርፍና ኪሳራ ከወዲሁ መገመትና ማመዛዘን ብልህነት ነው ። አዎን የዋህነት ሞኝነት አይደለም ። መታገስና መፍራት የተለያዩ ነገሮች ናቸው በትንሹ በትልቁ ከሰዎች ጋር መጋጨት ከመሀይማን ጋር መጣላትና መልስ መሰጣጠት የጥሩ አማኝ ባህሪ አይደለም ። ምንም ለነገሮች መስጠት የሚቻል ቢሆንም ሰምቶ መቻናልና ንቆ መተዉ ለበለጠ ዉጤት የሚያበቃ ከመሆኑም በላይ የበሳልነት ምልክት ነዉ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg