Skip to main content
ማህሌት ነኝ ሰለምቴዋ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ። እርሱም ወደ ተፈጠርኩበት እምነት እንድመለስ ያደረገኝ አጋጣሚ ቢኖር ። በአንድ አጋጣሚ የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ትምህርት ተፓስቶ አሳዛኝና አስለቃሽ ታሪክ የሚል አርእስት ተመለከትኩኝ እና ምንድን ነው ብዬ ቪድዮውን ከፍቼ ማድመጥ ጀመርኩኝ ። ከዚህ በፊት እኔ ለእሥልምና መጥፎ አመለካከት ያለኝ ልጅ አልነበርኩም ። ማለት እምነቱ ትክክል ነው የማለት እሳቤው ባይኖረኝም ግን የሰውን እምነት ስለማከብር ያለ እውቀት በሰዎች እምነት ላይ ድንበር ዘለልና ጥላቻን ያዘለ ቃላቶችን እና መጥፎ አመለካከት የለኝም ነበር ። ይህም የሰው እምነት ስለሆነ ክብር እሰጣለው ። ወደ ጀምሬ ልመለስና ቪድዮውን ማድመጥ ጀመርኩኝ ኡስታዝ ያሲን ሲናገር አይኖቹ ከእንባ አልደረቁም ነበር እያለቀሰ ታሪኩኝ ጀመረ ታሪኩ ሁሉን ነገር ጥሎ ወደ ነቢያችን ሥለ መጣ ሰው ነበር እርሱም የጆንያው ባለቤት የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን ያንን ጊዜ የእኔም ህይወት ተቀየረ ንግግሩን እያደመጥኩኝ በእንባ ታጅቤ አይኖቼ ያነባሉ ። ምንድን ነው ? አልኩኝ እራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ ማህሌት ምንድን ነው ያስለቀሰሽ ብዬ ውስጤን ጠየኩኝ የልቤ ትርታ ጨመረ ረሱልን ልቤ መፈለግና ማወቅ አሰበ በቃ ነገሮች ምትት አሉብኝ ። ስለ ጆንያው ባለቤት እዲህ እያለ ነበር ኡስታዝ ማውራት የጀመረው ፦ #የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን(ረ.ዐ) አጭር የህይወት ታሪክ ። እስልምናን በመቀበሉ ብቻ የለበሰውን ልብስ እንኳን ሳይቀር በአጎቱ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ ጆንያ ለብሶ የናፈቃቸውን ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለማግኘት ጉዞውን ወደ መዲና አደረገ ልክ መዲና ሲደርስ የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቤት በር ላይ ቆሞ የነሱ ከቤት መውጣት በናፍቆት ይጠባበቅ ጀመር ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከቤት ሲወጡ ባየ ጊዜ የደስታ እንባው ጉንጩ ላይ መፍሰስ ጀመረ የናፈቃቸውን ወዳጆቹን እና ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሶላት አሰግደው እንደጨረሱ እንደ ልምዳቸው ቆሙ እና ማን ሰገደ ማን ቀረ እያሉ የባልደረቦቻቸውን ፊት ማስተዋል ጀመሩ፦ ከዛ ይሄንን ወጣት አዩት ከየት ነው የመጣህ አንተ ወጣት ብለው ጠየቁት እርሱም ከሙዘይና ጎሳ ነው ሸሽቼ የመጣሁት አሏቸው፦ ነብዩ ስምህ ማነው አሉት አብዱል_ኡዛ(የኡዛ_ባርያ) እባላለሁ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተገርመው አዩት እና ይሄ የለበስከው ጆንያ ምንድነው ልብስ የለህም ብለው ጠየቁት፦ እርሱም አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አጎቴ በእርሶ መስለሜን ባወቀ ጊዜ ያለኝን ንብረቴን ሁሉ ቀማኝ ከነዚህ ጆንያዎች ውጪ ምንም አላገኘሁም አንተን ለመገናኘት ስል ላይ እና ታች አስሬ ወደ አንተ መጣሁ የአላህ መልእክተኛ አሏቸው፦ ነቢዩ ﷺ ይህንን አደረክ እንዴ አንተ ለአላህ እና መልእክተኛው ስትል ንብረትህን ጥለህ መጣ አላህ በነዚህ ሁለት ጆንያዎች ልብስ ይስጥህ ጀነት ውስጥ የፈለከውን እየበላህ የፈለከውን ለብሰህ ኑር በጀነት ውስጥ አንተ ከአሁን በኋላ #አብዱል_ኡዛ አይደለህም #ዙል_ቢጃደይን ነህ የጆንያዎች ባለቤት ነው ስምህ ። ኡላሞች ይሄ ሰው የውመል ቂያማ መክሉቃታ በአላህ ፊት በቆመበት ፊት ይጠራል አንተ ዙል ቢጃደይን ውጣ ወደ አላህ ይባላል ። ዙል ቢጃደይን ንብረቱን ሁሉ ነገሩን ትቶ ወደ ነቢዩ ﷺሸሸ እራቁቱን እሳቸው ጋር ተገናኘ አህለ ሶፋ የሚባሉ ነቢዩ ﷺሶሃባዎች ደሀዎች ከነብዩ ቤት ጀርባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ ከነሱ ጋር መኖር ጀመረ ይሄ ሶሃባ ። አብዱል ኡዛ የዛሬው አድሱ ስሙ አብደላህ ዙል ቢጃደይን ይባላል አብደላህ ከሰለመ በኋላ የአላህ ሱብሃናሁ ወተአላ ትልቅ ባርያ ሆነ ከኢባዳዎቹ ውስጥ በጣም ዱዓ እና ዚክር ያበዛ ነበር፦ ተመላሹ ተፀፃቹ ብለው ነበር ስሙን የሚጠሩት ሌላው ባህሪው ቁርአን መቅራት በጣም ያበዛ ነበር ። በቃ ይህንን ታሪክ ካደመጥኩኝ በኋላ ውስጤ ተረበሸ ማድመጥም ማንበብም አለብኝ ብዬ ተነሳሁኝ ነገሮችን ትኩረት ሰጥቼ በሃይማኖት ትምህርት ላይ ትኩረት አደረኩኝ አሏህ የኡስታዝን ንግግር ሰበብና የማንቂያ ደውል አደረገልኝ እኔም ብዙዎችን የሃይማኖት ስብከትን እና ከማንበብ ከማድመጥ በኋላ ወደ ተፈጠርኩበት እምነት ብሸሃዳተይን ገባሁኝ ። አሁን አልሃምዱሊላህ የተረጋጋ መንፈስ እና ደስ የሚል ህይወት ውስጥ ነው ። መልእክት ቢኖረኝ አንብቡ ትምህርቶችን አድምጡ ከእውቀት ጋር እውነትም ትገለጥላችኃለች ነው 🙏 አሏህ ከፈቀደና ነገሮች ሲመቻቹልኝ በድምጽ በደንብ አድርጌ ታሪኬን ላካፍላችሁ እወዳለሁ ። ኢንሻሏህ ✍️ https://t.me/joinchat/RXYpviFTL70OQdu2 አሁንም ባለ ታሪክ ለሆኑ ሰለምቴዎች በራችን ክፍት ነው ይላል የአስሓቡል የሚን ጀመዐ ። ሰለምቴዎችን እንጋብዛለን ። እርሶ ሰለምቴ ኖት..!? እንግዲያውስ ታሪኮ ለሌሎች መማሪያ ይሆን ዘንድ ። ለአንዲት ነፍስ የሒዲያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ታሪኮን ያካፍሉን ። አድራሻችን ፦ የሰለምቴዎች ግሩፕ http://t.me/Selmeta ቴሌግራም 00966597257492 http://t.me/Ohanw9 00966503917209 http://t.me/OBintMahmud በዋትስ-አፕ 00966554225870 https://t.me/Quran_is_life_Sari_A ቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/AshaBuleyamine የፕሮግራሙ መገኛ ዩቱብ፦ https://m.youtube.com/watch?v=ssov6TY3yzc&feature=youtu.be ሠለምቴ የሆኑ ይምጡ ለመሥለም የሒዳያ ሠበበዎን ያካፋሉን! እኛም ለሌሎች አሥተማሪ በሆነ መልኩ እያዘጋጀን እናቀርባለን።
Popular posts from this blog
Comments
Post a Comment