Posts
ጉዞ ወደ ኢሥላም ❤️ አልሃምዱሊሏህ እህታችን በሸሃዳተይን ወደ እሥልምና ገብታለች
- Get link
- Other Apps
ከወንድም አቡበከር ትረካ የተወሰደ አቢ ደምደም ማን ነው ? እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማን ነዉ?? _________ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው የብዙዎቻችሁ ጥያቄ እንደሚሆን እገምታለሁ ተከተሉኝማ ልንገራችሁ። አቡ ዳዉድና ጦብራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድያላሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸዉ ከእናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን የሚችል ማነው ?? በማለት ጠየቋቸው ሰሀቦችም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አቢ ደምደም ደግሞ ማነው በማለት በግርምት ጠየቋቸው ። እሱማ አሉ ነብያችን ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት ጌታየ ሆይ እኔ ነብሴና ክብሬን ሰጥቸሀለሁ የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሰድብም። የበደሉትን አይበድልም የሚመቱትንም መልሶ አይመታም አሏቸው የአቢ ደምደምና የአባታችን አደም አለይሂ ሰላም ልጅ ታሪካቸው ተመሳሳይነት አለው። ወንድሙ ሊገድለው በዛተበት ወቅት እንዲህ በማለት ነበር የመለሰለት ። ልትገድለኝ እጅህን ወደኔ ብትዘረጋ እኔ ልገድልህ እጀን ወደ አንተ የምዘረጋ አይደለሁም እኔ የአለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁና አለ ። አቢ ደምደም ታሪኩ አጭር ቢሆንም ከስብዕናው የምናገኘው መልዕክት ግን ግዙፍ ነው በዋናነት ከምፅዋት ወይም ሰደቃ ምንም የሚሰጠው ነገር የለለው ሰው ስምና ክብሩን አሳልፎ በመስጠት ብቻ እሱን ያሙ ሰዎች ወንጀል ዉስጥ እንዳይወድቁ ዋስትናን ሊሰጣቸው እንደሚችልም እንማራለን ። ቢያሙኝም በኔ ምክንያት መጠየቅ የለባቸውም ስጋየ ለነሱ ሀላል ነዉ የሚል ይመስላል አቢ ደምደም። ወዳጆቸ በኔ ምክንያት አንድም ሰዉ መጠየቅ የለበትም ማለት ምንኛ ለሰው ልጅ ማዘንና መቆርቆር ነዉ። የዘመናችን የሰብዓዊ መብት ታጋዮችስ ይህን ያህል ተጉዘው ይሆን? ብቻ የአቢ ደምደም ነገር ይገርማል በምፅዋት ወይም ልግስና ዙሪያ ታዋቂው ኢማም ኢብኑል ቀዩም ሲናገሩ ልግስና አስር ደረጃዎች አሉት ካሉ በኋላ ከነዚህ መካከል የራስን ክብርና ስም መስጠትን በሰባተኛ ደረጃ ላይ ቆጥረዋል ። ወዳጆቼ ሆይ የአቢ ደምደምን ሁኔታ ሳስበው ዉስጡ እንዲህ የሚል መሰለኝ ጌታየ ሆይ ሰዎች ሁሉ ከገንዘብ እና ንብረት የሚለግሱት ነገር አላቸው እኔ ግን የምሰጠውም የምለግሰዉም ነገር የለኝምና ይህንኑ ስጦታየን ተቀበለኝ የሰደበኝና ያማኝን ሰዉ ሁሉ ነፃ ነህ ዕዳ የለብህም በኔ ምክንያት አትቀጣም ብየዋለሁ ። ታዲያ ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም በአቢ ደምደም ሁኔታ በመደነቅ ይመስላል ማነው ከእናንተ ዉስጥ መሆን የሚችለው በማለት የሚጠይቁት በእርግጥ ነገሩ አላህ ሱበሀነወ ተአላ ላገራለት ሰው ካልሆነ በስተቀር እጅግ ከባድ ነው ። ወዳጆቸ ሆይ አንዳንድ ጊዜ ባላሰብነዉ መልኩ ከግብራችን ጋር የማይዛመዱ ስም ሊሰጠን ይችላል ለማስተካከል ስንወድቅ ስንነሳ ለድናችን ስንሮጥ ለዑማዉ ስንታትር ስንፅፍ ስንናገር ስንከራከር ፈፅሞ የማይመስልና ያልጠበቅነውን ነገር ልንባል እንችላለን ። ያላንዳች ጥቅም የማንሮጥ ተደርጎም ሊወራብን ይችላል እዉነተኛ የአላህን ዉዴታ ፈልገንና ለድኑ አስበን የምንሰራ ከሆነ ምንም እንኳን የሚወጡልንና የሚሰጡን ስሞች ከባድ አሳማሚና አስደንጋጭ ቢሆኑም ፈፅሞ ልንሸበር አይገባም ባይሆን እንደ አቢ ደምደም እንሁን ። የሰደበንን መልሰን አንስደብ የበደለንን አንበድል የመታንን ለመምታት አንጋበዝ ከማሀይማን ጋር ጊዜ አናጥፋ። እነሱ አላወቁም ና ይቅር እንበላቸው ያኔ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም አለም ስኬት እንጎናፀፋለን ። እንደ አቢ ደምደም እንሁን ሰው እንዲህ አለኝ ብለን አንጨነቅ ሰዉ ስላለ አይሙቀን ሰዉ ስላላለም አይብረደን ደረታችን ትግስታችን ፅናታችን ይቅርታችን ሰፊ ይሁን ። የበደሉን ሰዎች ካሉ የመጀመሪያዎቹ ተጎጅዎች እነሱ ራሳቸው ናቸውና እንዘንላቸዉ። ላጠፉብን ይቅር እንበላቸው ከይቅርታ በላይ ጣፋጭ ነገር የለምና ወዳጆቸ ሆይ ከድርጊት በፊት የነገሮችን ትርፍና ኪሳራ ከወዲሁ መገመትና ማመዛዘን ብልህነት ነው ። አዎን የዋህነት ሞኝነት አይደለም ። መታገስና መፍራት የተለያዩ ነገሮች ናቸው በትንሹ በትልቁ ከሰዎች ጋር መጋጨት ከመሀይማን ጋር መጣላትና መልስ መሰጣጠት የጥሩ አማኝ ባህሪ አይደለም ። ምንም ለነገሮች መስጠት የሚቻል ቢሆንም ሰምቶ መቻናልና ንቆ መተዉ ለበለጠ ዉጤት የሚያበቃ ከመሆኑም በላይ የበሳልነት ምልክት ነዉ። https://t.me/joinchat/AAAAAEV2Kb4hUy-9DkHbtg
- Get link
- Other Apps
ለእሥልምና ትልቅ ጥላቻ ነበረኝ ያለው ሰለምቴው አባስ በባጢል ላይ ያሳለፋቸው ጊዜኣቶች እየተቆጨባቸው ወደ ኢሥላም በመምጣቱ በሐሴት ተሞልቶ የእሥልምናን ጣፋጭ መዓዛ እየናገረ ዛሬ በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ላይ ከወንድም ሙሐመድ ጋር ቆይታውን በማድረግ ድንቅ ታሪኩን አካፍሎናል ። 👇 https://m.youtube.com/watch?v=2QFdvrYfr3k&feature=youtu.be የሰለምቴዎች የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በአዲስ ታሪክ ከአዲስ እንግዳ ጋር ይቀጥላል......... AS-HABULE YAMLNE TUBE https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q
- Get link
- Other Apps